ሉቃስ 8:40 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡም ሁሉ እየጠበቁት ስለ ነበር ኢየሱስ በተመለሰ ጊዜ ተቀበሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡ ሁሉ መምጣቱን ይጠባበቁ ስለ ነበር፣ ኢየሱስ በተመለሰ ጊዜ በደስታ ተቀበሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡ ይጠባበቀው ስለ ነበር ኢየሱስ ተመልሶ በመጣ ጊዜ ሁሉም በደስታ ተቀበሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስም በተመለሰ ጊዜ ሕዝቡ በአንድነት ተቀበሉት፤ ሁሉ ይጠባበቁት ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም በተመለሰ ጊዜ ሁሉ ይጠብቁት ነበርና ሕዝቡ ተቀበሉት። |
ምክንያቱም ዮሐንስ ጻድቅና ቅዱስ ሰው መሆኑን ሄሮድስ በማወቁ ይፈራውና ይጠብቀው ነበር። ዮሐንስ የሚናገረውን ሲሰማ ሄሮድስ ቢታወክም በደስታ ያዳምጠው ነበር።
“ወደ ቤትህ ተመለስ፤ እግዚአብሔር እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረግልህ ተናገር።” እርሱም በመላው ከተማ ኢየሱስ እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረገለት እየሰበከ ሄደ።
ስለዚህ ያንጊዜ ወደ አንተ ላክሁ፤ አንተም በመምጣትህ መልካም አድርገሃል። እንግዲህ አንተ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዝኸውን ሁሉ እንድንሰማ እኛ ሁላችን አሁን በእግዚአብሔር ፊት በዚህ አለን።”