ሉቃስ 23:53 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አውርዶም በቀጭን ሐር ልብስ ከፈነው፤ ማንም ገና ባልተቀበረበት ከዓለትም በተወቀረ መቃብር አኖረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተፈቀደለትም ጊዜ፣ ሥጋውን አውርዶ በበፍታ ከፈነው፤ ከድንጋይ ተፈልፍሎ በተሠራና ገና ማንም ባልተቀበረበት መቃብር ውስጥ አስቀመጠው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አስከሬኑንም አውርዶ በቀጭን ሐር ልብስ ከፈነው፤ ማንም ሰው ባልተቀበረበት ከአለት ተወቅሮ በተዘጋጀ መቃብር ውስጥ ቀበረው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሥጋውንም አውርዶ በበፍታ ገነዘው፤ ማንም ባልተቀበረበት፥ ከድንጋይም በተፈለፈለ መቃብር ቀበረው፤ ታላቅ ድንጋይም አንከባልሎ መቃብሩን ገጥሞ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አውርዶም በተልባ እግር ልብስ ከፈነው፥ ማንም ገና ባልተቀበረበት ከዓለትም በተወቀረ መቃብር አኖረው። |