ሉቃስ 21:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህ ሁሉ ከትርፋቸው ወደ መዝገቡ አስቀምጠዋልና፤ እርሷ ግን እየጐደላት የነበራትን ንብረት ሁሉ ሰጠች፤” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ ሰዎች የሰጡት ከትርፋቸው ላይ ሲሆን፣ እርሷ ግን የሰጠችው ከጕድለቷ ያላትን መተዳደሪያዋን በሙሉ ነው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ የሰጡት ከሀብታቸው የተረፋቸውን ነው፤ እርስዋ ግን ድኻ ሆና ሳለች ምንም ሳታስቀር ያላትን ሁሉ ሰጠች።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህ ሁሉ ከተረፋቸው ለእግዚአብሔር መባ አግብተዋልና፤ ይህቺ ግን ከድህነቷ ያላትን ጥሪቷን ሁሉ አገባች።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህ ሁሉ ከትርፋቸው ወደ እግዚአብሔር መዝገብ ጥለዋልና፤ ይህች ግን ከጕድለትዋ የነበራትን ትዳርዋን ሁሉ ጣለች አለ። |
ከዐሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም የሚፈሳት ሴት ነበረች፤ ያላትንም ንብረት ሁሉ ተጠቅማ ለባለመድኃኒቶች ብታውልም ማንም ሊፈውሳት አልተቻለውም።