ሉቃስ 21:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰማያት ኀይላት ይናወጣሉና፥ ሰዎችም ከፍርሃትና በዓለም ላይ የሚመጣውን ከመጠበቅ የተነሣ ይደክማሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰማያት ኀይላት ስለሚናወጡ፣ ሰዎች በፍርሀትና በዓለም ላይ ምን ይመጣ ይሆን እያሉ በመጠባበቅ ይዝላሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዓለም ላይ የሚመጣውን ነገር በመጠባበቅ ሰዎች በፍርሃት ይሸበራሉ፤ በዚያን ጊዜ የሰማይ ኀይሎች ይናወጣሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዓለም ላይ ከሚመጣው ፍርሀትና ሽብር የተነሣም የሰዎች ነፍስ ትዝላለች፤ ያንጊዜ የሰማያት ኀይል ይናወጣልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰዎችም ከፍርሃትና በዓለም የሚመጣበትን ከመጠበቅ የተነሣ ይደክማሉ፤ የሰማያት ኃይላት ይናወጣሉና። |
በጠላቶቻቸውም ምድሮች ሳሉ ከእናንተ መካከል በተረፉት ላይ በልባቸው ድንጋጤን እልክባቸዋለሁ፤ በነፋስም የምትንቀሳቀስ የቅጠል ድምፅ ታስደነብራቸዋለች፤ እነርሱም ከሰይፍ እንደሚሸሹ ይሸሻሉ፤ ማንም ሳያሳድዳቸው ይወድቃሉ።
“ከነዚያ ቀናት መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያት ኃይሎችም ይናወጣሉ።