ሉቃስ 19:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታዲያ ገንዘቤን ለገንዘብ ለዋጮች አደራ ያልሰጠኸው ለምንድን ነው? እኔም መጥቼ ከነትርፉ እወስደው ነበር፤’ አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መጥቼ ገንዘቤን ከነትርፉ እንድወስድ፣ ለምን ለሚሠሩበት ሰዎች አልሰጠህም?’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ ገንዘቤን ትርፍ በሚያስገኝልኝ በባንክ ለምን አላስቀመጥከውም ነበር? እኔ ተመልሼ ስመጣ ከነትርፉ እወስደው ነበር’ አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለምን ገንዘቤን ወደ ለዋጮች አላስገባህም? እኔም መጥቼ ከትርፉ ጋር በወሰድሁት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም መጥቼ ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር አለው። |
እርሱም ‘አንተ ክፉ አገልጋይ፥ አፍህ በተናገረው እፈርድብሃለሁ። እኔ ያላስቀመጥኩትን የምወስድና ያልዘራሁትን የማጭድ ጨካኝ ሰው እንደሆንሁ አወቅህ፤