ሉቃስ 19:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም ይህን ሲሰሙ ሳለ፥ ወደ ኢየሩሳሌም በመቃረቡ፥ የእግዚአብሔርም መንግሥት ፈጥኖ እንደሚገለጥ ይገምቱ ነበርና፥ ተጨማሪ ምሳሌ ነገራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡ ይህን እየሰሙ ሳሉ፣ በምሳሌ መናገሩን ቀጠለ፤ ምክንያቱም ወደ ኢየሩሳሌም በመቃረቡና ሰዎቹም የእግዚአብሔር መንግሥት የሚገለጥ ስለ መሰላቸው ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎቹ ይህን በመስማት ላይ ሳሉ ኢየሱስ አንድ ምሳሌ ደግሞ ነገራቸው፤ እርሱ ወደ ኢየሩሳሌም ስለ ተቃረበ ሰዎቹ የእግዚአብሔር መንግሥት አሁኑኑ የምትገለጥ መስሎአቸው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንም ሲሰሙ፤ ምሳሌ መስሎ ነገራቸው፤ ወደ ኢየሩሳሌም ቀርቦ ነበርና፤ እነርሱም የእግዚአብሔር መንግሥት ወዲያውኑ የምትገለጥ መስሎአቸው ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ይህን ሲሰሙ፥ ወደ ኢየሩሳሌም መቅረቡ ስለ ሆነ የእግዚአብሔርም መንግሥት ፈጥኖ ሊገለጥ እንዳለው ስለ መሰላቸው ምሳሌ ጭምር ተናገረ። |