በአክዓብ ዘመነ መንግሥት ሒኤል ተብሎ የሚጠራ የቤትኤል ተወላጅ ኢያሪኮን መልሶ ሠራ፤ ጌታ በነዌ ልጅ በኢያሱ አማካይነት አስቀድሞ በተናገረው ቃል መሠረት ሒኤል የኢያሪኮን የመሠረት ድንጋይ በሚያኖርበት ጊዜ የበኩር ልጁ አቢራም ሞተበት፤ የቅጽርዋንም በሮች በሚሠራበት ጊዜ ታናሹ ልጁ ሠጉብ ሞተ።
ሉቃስ 19:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ኢያሪኮም ገብቶ በዚያ በኩል አልፎ እየሄደ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ወደ ኢያሪኮ ገብቶ በዚያ ዐልፎ ይሄድ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ወደ ኢያሪኮ ከተማ ገብቶ በዚያ በኩል አልፎ እየሄደ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስም ወደ ኢያሪኮ ገብቶ በዚያ ያልፍ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ኢያሪኮም ገብቶ ያልፍ ነበር። እነሆም ዘኬዎስ የሚባል ሰው፥ እርሱም የቀራጮች አለቃ ነበረ፥ ባለ ጠጋም ነበረ። |
በአክዓብ ዘመነ መንግሥት ሒኤል ተብሎ የሚጠራ የቤትኤል ተወላጅ ኢያሪኮን መልሶ ሠራ፤ ጌታ በነዌ ልጅ በኢያሱ አማካይነት አስቀድሞ በተናገረው ቃል መሠረት ሒኤል የኢያሪኮን የመሠረት ድንጋይ በሚያኖርበት ጊዜ የበኩር ልጁ አቢራም ሞተበት፤ የቅጽርዋንም በሮች በሚሠራበት ጊዜ ታናሹ ልጁ ሠጉብ ሞተ።
ከዚህ በኋላ ወደ ኢያሪኮ መጡ። ኢየሱስና ደቀመዛሙርቱ ከብዙ ሕዝብ ጋር ከኢያሪኮ ሲወጡ ዐይነ ስውሩ የጤሜዎስ ልጅ በርጤሜዎስ በመንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን ነበር።
የነዌም ልጅ ኢያሱ ከሰጢም ሁለት ሰላዮች በስውር እንዲህ ብሎ ላከ፦ “ሄዱ፥ ምድሪቱንና ኢያሪኮን እዩ።” ሄዱም፤ ረዓብም ወደሚሉአት አመንዝራ ቤት ገቡ፥ በዚያም አደሩ።