ያዘዘውን ስላደረገ ያንን አገልጋይ ያመሰግነዋልን?
እንግዲህ ይህ ሰው፣ ባሪያው የታዘዘውን በመፈጸሙ መልሶ ያመሰግነዋልን?
ታዲያ፥ አገልጋዩ የታዘዘውን ስለ ፈጸመ ጌታው የሚያመሰግነው ይመስላችኋልን?
እንግዲህ ጌታው ያዘዘውን ሥራውን ቢሠራ ለዚያ አገልጋይ ምስጋና አለውን?
ያንን ባሪያ ያዘዘውን ስላደረገ ያመሰግነዋልን?
እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ ‘የማንጠቅም አገልጋዮች ነን፤ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል፤’ በሉ።”
‘የምበላውን እራቴን አሰናዳልኝ፤ እስክበላና እስክጠጣ ድረስ ታጥቀህ አገልግለኝ፤ በኋላም አንተ ብላና ጠጣ፤’ ይለው የለምን?