ሉቃስ 17:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም ‘እነሆ በዚህ’ ወይም ‘እነሆ በዚያ’ ይሉአችኋል፤ አትሂዱ፤ አትከተሉአቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎች፣ ‘እዚያ ነው’ ወይም ‘እዚህ ነው’ ይሏችኋል፤ ተከትላችኋቸውም አትሂዱ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎች ‘እነሆ፥ ክርስቶስ እዚህ ነው! ወይም እዚያ ነው!’ ይሉአችኋል፤ ነገር ግን አትሂዱ፤ አትከተሉአቸውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ በዚህ ነው፥ ወይም እነሆ፥ በዚያ ነው ቢሉአችሁ አትውጡ፤ አትከተሉአቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም፦ እነሆ በዚህ፥ ወይም፦ እነሆ በዚያ ይሉአችኋል፤ አትሂዱ አትከተሉአቸውም። |