እነርሱም እየጮኹ “ኢየሱስ ሆይ! መምህር ሆይ! ማረን፤” አሉ።
በታላቅ ድምፅ፣ “ኢየሱስ፤ ጌታ ሆይ፤ ራራልን!” አሉት።
ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው “ኢየሱስ ሆይ፥ መምህር ሆይ፥ እባክህ ማረን!” እያሉ ጮኹ።
ድምጻቸውንም ከፍ አድርገው፥ “ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ እዘንልን” አሉ።
እነርሱም እየጮኹ፦ ኢየሱስ ሆይ፥ አቤቱ፥ ማረን አሉ።
እነሆ አንዲት ከነዓናዊት ሴት ከዚያ አገር መጥታ “የዳዊት ልጅ ጌታ ሆይ ማረኝ፤ ሴት ልጄ በጋኔን ክፉኛ ተይዛለች” እያለች ጮኸች።
ኢየሱስ ከዚያ አልፎ ሲሄድ ሁለት ዓይነ ስውሮች “የዳዊት ልጅ ሆይ! ማረን፤” ብለው እየጮሁ ተከተሉት።
ሊገድለው ፈልጎ ብዙ ጊዜ እሳትም ውስጥ ውሃም ውስጥ፥ ይጥለዋል፤ የሚቻልህ ከሆነ ራራልን፤ ርዳንም።”
አይቶም “ሂዱ፤ ራሳችሁን ለካህናት አሳዩ፤” አላቸው።
ስምዖንም መልሶ፦ “አቤቱ! ሌሊቱን ሙሉ ብንደክምም ምንም አልያዝንም፤ ነገር ግን በቃልህ መረቦቹን እጥላለሁ፤” አለው።