እናንተም የምትበሉትን የምትጠጡትንም አትፈልጉ፤ አታወላውሉም፤
ስለዚህ ምን እንደምትበሉና ምን እንደምትጠጡ አትሹ፤ አትጨነቁም፤
“ስለዚህ ‘ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን?’ እያላችሁ በማሰብ አትጨነቁ።
እናንተም የምትበሉትንና የምትጠጡትን አትፈልጉ፤ ወዲያና ወዲህም አትበሉ፤ አትጨነቁለትም።
እናንተም የምትበሉትን የምትጠጡትንም አትፈልጉ፥ አታወላውሉም፤
ስለዚህ “ምን እንበላለን? ምን እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን?” ብላችሁ አትጨነቁ፤
ለደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አለ “ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ለነፍሳችሁ በምትበሉት ወይም ለሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ።
እንግዲህ ትንሹን ነገር ስንኳ የማትችሉ ከሆናችሁ፥ ስለምን በሌላ ትጨነቃላችሁ?
ይህንስ ሁሉ በዓለም ያሉ አሕዛብ ይፈልጉታልና፤ የእናንተም አባት ይህ እንዲያስፈልጋችሁ ያውቃል።
ከዚያም፥ “ያለ ቦርሳና ያለ ከረጢት፥ ያለ ጫማም በላክኋችሁ ጊዜ፥ የጐደለባችሁ ነገር ነበርን?” አላቸው። እነርሱም “ምንም” አሉ።