ሉቃስ 12:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ትንሹን ነገር ስንኳ የማትችሉ ከሆናችሁ፥ ስለምን በሌላ ትጨነቃላችሁ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ቀላሉን ነገር እንኳ ማድረግ የማትችሉ ከሆነ፣ ስለ ሌላው ነገር ለምን ትጨነቃላችሁ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ ይህን ትንሹን ነገር እንኳ ማድረግ የማትችሉ ከሆናችሁ፥ ስለምን በሌላው ነገር ትጨነቃላችሁ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህን ቀላሉን የማትችሉ ከሆነ በሌላው ለምን ትጨነቃላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ ትንሹን ነገር ስንኳ የማትችሉ ከሆናችሁ፥ ስለ ምን በሌላ ትጨነቃላችሁ? |
ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ስለ ነፍሳችሁ ምን እንደምትበሉና ምን እንደምትጠጡ፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ ምን እንደምትለብሱ አትጨነቁ፤ ነፍስ ከምግብ ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?
አበቦችን እንዴት እንዲያድጉ ተመልከቱ፤ አይደክሙም፤ አይፈትሉምም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፤ ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩ ሁሉ ከእነዚህ እንደ አንዲቱ አለበሰም።