ሉቃስ 1:53 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቦአል፤ ሀብታሞችን ባዶአቸውን ሰዶአቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቧቸዋል፤ ሀብታሞችን ግን ባዷቸውን ሰድዷቸዋል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተራቡትን በመልካም ነገር አጥግቦአቸዋል፤ ሀብታሞችን ግን ባዶ እጃቸውን ሰዶአቸዋል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተራቡትን ከበረከቱ አጠገባቸው፤ ባለጠጎችንም ባዶ እጃቸውን ሰደዳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቦአል፤ ባለ ጠጎችንም ባዶአቸውን ሰዶአቸዋል። |
ወንድሞች ሆይ! መጠራታችሁን ተመልከቱ፤ እንደ ሰው መመዘኛ ብዙዎች ጥበበኞች አልነበሩም፥ ብዙዎች ኀያላን አልነበሩም፥ ብዙዎች ታላላቅ ሰዎች አልነበሩም።
አሁንማ ሞልቶላችኋል! አሁንማ ሀብታሞች ሆናችኋል! ያለ እኛ ነግሣችኋል! እኛም ከእናንተ ጋር እንድንነግሥ፥ በእርግጥ ብትነግሡ ኖሮ፥ መልካም በሆነ!