ዘሌዋውያን 3:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለቁርባኑ ጠቦትን ቢያቀርብ በጌታ ፊት ያቀርበዋል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም መሥዋዕቱ የበግ ጠቦት ከሆነም፣ በእግዚአብሔር ፊት ያምጣው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ሰው የሚያቀርበው መባ የበግ ጠቦት ቢሆን፥ በእግዚአብሔር ፊት ያቅርበው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለቍርባኑ የበግ ጠቦትን ቢያቀርብ በእግዚአብሔር ፊት ያቀርበዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለቍርባኑ ጠቦትን ቢያቀርብ በእግዚአብሔር ፊት ያቀርበዋል፤ |
ቁርባኑን ለማቅረብ የሚያመጣ ሰው የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ በሆነ ዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ አንድ እጅ የሆነ መልካም ዱቄትን የእህል ቁርባን አድርጎ ለጌታ ያቅርብ፤
ክርስቶስም እንዳፈቀራችሁ፥ ስለ እናንተም ለእግዚአብሔር መልካም መዓዛ ያለው መባንና መሥዋዕት አድርጎ ራሱን አሳልፎ እንደሰጠ፥ በፍቅር ተመላለሱ።
ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበው የክርስቶስ ደም እንዴት ልቆ፥ ሕያው እግዚአብሔርን ለማምለክ፥ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን!