ዘሌዋውያን 13:54 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑ ደዌ ያለበን ነገር እንዲያጥቡ ያዝዛል፤ ሌላም ሰባት ቀን ለይቶ ያስቀምጠዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑ ደዌው ያለበት ነገር እንዲታጠብ ይዘዝ፤ ዕቃውንም ሰባት ቀን ደግሞ ያግልል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልብሱ በውሃ ታጥቦ እስከ ሰባት ቀን ድረስ ለብቻ እንዲቀመጥ ያድርግ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑ ደዌ ያለበቱ ነገር እንዲታጠብ ያዝዛል፤ ሌላም ሰባት ቀን ይለየዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑ ደዌ ያለበቱ ነገር እንዲታጠብ ይዘዝ፤ ሌላም ሰባት ቀን ይዘጋበታል። |
ደዌው ያለበት ነገር ከታጠበ በኋላ ካህኑ ያየዋል፤ እነሆም፥ ደዌው ባይሰፋ ነገር ግን መልኩን ባይለውጥ፥ እርሱ ርኩስ ነው፤ በእሳት አቃጥለው፤ የለምጽ ደዌው ምልክቱ በውስጥ ወይም በውጭ ቢሆን እየሰፋ የሚሄድ ደዌ ነው።