ልብን የሚያሸብር መራር ኀዘን ደርሶባቸው፥ ከማንም ሰው ወይም ከሕዝብህ እስራኤል ወደዚህ ቤተ መቅደስ እጃቸውን በመዘርጋት በሚጸልዩበት ጊዜ፥
ዘሌዋውያን 13:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለምጹም በቆዳው ላይ ሰፍቶ ቢወጣ፥ ካህኑ ማየት እስከሚችልበት አካል የለምጹ ደዌ የታመመውን ሰው ቆዳ ሁሉ ከራሱ እስከ እግሮቹ ድረስ ቢሸፍነው፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ደዌው በአካላቱ ሁሉ ላይ በመውጣት በሽተኛውን ከራስ ጠጕር እስከ እግር ጥፍር ያለበሰው መሆኑን ካህኑ እስካየ ድረስ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ ካህኑ አስተያየት የሥጋ ደዌው በሽታ ሰውየውን ከእግር ጥፍሩ እስከ ራስ ጠጒሩ የሸፈነው ከሆነ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለምጹም በቆዳው ላይ ሰፍቶ ቢወጣ፥ ለምጹም የታመመውን ሰው ቆዳውን ሁሉ ከራሱ እስከ እግሮቹ ድረስ እንደ ከደነው ለካህኑ ቢመስለው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለምጹም በቁርበቱ ላይ ሰፍቶ ቢወጣ፥ ለምጹም የታመመውን ሰው ቁርበቱን ሁሉ ከራሱ እስከ እግሮቹ ድረስ እንደ ከደነው ላካህኑ ቢመስለው፥ ካህኑ ያያል፤ |
ልብን የሚያሸብር መራር ኀዘን ደርሶባቸው፥ ከማንም ሰው ወይም ከሕዝብህ እስራኤል ወደዚህ ቤተ መቅደስ እጃቸውን በመዘርጋት በሚጸልዩበት ጊዜ፥
ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል።
ካህኑ ያያል፤ እነሆም፥ የለምጹ ደዌ ሰውነቱን ሁሉ ቢሸፍነው የታመመውን ሰው፦ ንጹሕ ነው ይለዋል፤ ሰውነቱ ሁሉ ፈጽሞ ተለውጦ ነጭ ሆኖአል፤ ንጹሕ ነው።