የሸክለኛ ማድጋ እንደሚሰበር ይሰብረዋል፥ ሳይራራም ያደቀዋል፤ ከስባሪውም እሳት ከማንደጃ የሚወስዱበት፥ ወይም ውኃ ከጉድጓድ የሚቀዱበት ገል አይገኝም።
ሰቈቃወ 4:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤት። ጥሩ ወርቅ የሚመስሉ የከበሩ የጽዮን ልጆች፥ የሸክላ ሠሪ እጅ እንደሠራው እንደ ሸክላ ዕቃ እንዴት ተቈጠሩ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ወርቅ ይቈጠሩ የነበሩ፣ የከበሩ የጽዮን ወንዶች ልጆች፣ የሸክላ ሠሪ እጅ እንደ ሠራው፣ እንዴት አሁን እንደ ሸክላ ዕቃ ሆኑ! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የከበሩ የጽዮን ልጆች እንደ ንጹሕ ወርቅ ያኽል ውድ ነበሩ፤ እንዴት አሁን የሸክላ ሠሪ እጅ እንደ ሠራው እንደ ሸክላ ዕቃ ተቈጠሩ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቤት። ጥሩ ወርቅ የሚመስሉ የከበሩ የጽዮን ልጆች፥ የሸክላ ሠሪ እጅ እንደ ሠራው እንደ ሸክላ ዕቃ እንዴት ተቈጠሩ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቤት። ጥሩ ወርቅ የሚመስሉ የከበሩ የጽዮን ልጆች፥ የሸክላ ሠሪ እጅ እንደ ሠራው እንደ ሸክላ ዕቃ እንዴት ተቈጠሩ! |
የሸክለኛ ማድጋ እንደሚሰበር ይሰብረዋል፥ ሳይራራም ያደቀዋል፤ ከስባሪውም እሳት ከማንደጃ የሚወስዱበት፥ ወይም ውኃ ከጉድጓድ የሚቀዱበት ገል አይገኝም።
እንዲህም ትላቸዋለህ፦ ‘የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ የሸክላ ሠሪው ዕቃ እንደሚሰባበር ዳግመኛም ሊጠገን እንደማይችል፥ እንዲሁ ይህን ሕዝብና ይህችን ከተማ እሰብራለሁ፤ የሚቀብሩበትም ስፍራ ሌላ የለምና በቶፌት ይቀበራሉ።
በውኑ ይህ ሰው ኢኮንያን የተናቀና የተሰበረ የሸክላ ዕቃ ነውን? ወይስ እርሱ ማንም የማይፈልገው የሸክላ ዕቃ ነውን? እርሱና ዘሩስ በማያውቋት ምድር ስለምን ተወርውረው ተጣሉ?
ይሁዳን እንደ ደጋኔ አጥፌዋለሁ፥ ኤፍሬምንም ቀስቱን አድርጌ አዘጋጅቻለሁ፤ ጽዮን ሆይ፥ ልጆችሽን በግሪክ ልጆች ላይ አስነሣለሁ፥ እንደ ተዋጊ ሰይፍም አደርግሻለሁ።
በአንድ ትልቅ ቤት ውስጥ የወርቅና የብር ዕቃዎች ብቻ ሳይሆኑ የእንጨትና የሸክላ ዕቃዎችም ደግሞ ይኖራሉ፤ እኩሌቶቹም ለክብር፥ እኩሌቶቹም ለውርደት ይሆናሉ፤