መጽሐፈ ዮዲት 9:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአባቴ የስምዖን አምላክ ጌታ ሆይ! የድንግሊቱን ማኅጸን በመፍታት ላረከሱአት፥ ጭኗን በመግለጥ ላሳፈሩአት፥ ማኅጸኗን በማርከስ ላዋረዷት፥ ይበቀል ዘንድ ለመጻተኛ ሰይፍን ሰጠህን፤ አንተ “አይሆንም” ብለህ ነበር፥ እነርሱ ግን አደረጉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በማኅፀን ያለ ጽንስን ያጠፉ፥ ድንግልንም ያጐሰቈሉ፥ ልብሷንም የገፈፉ፥ በከተማም በአራቱ ማዕዘን ለመገዳደር ማኅፀንን ያሳደፉ ጠላቶችን ይበቀል ዘንድ በእጁ ሰይፍን የሰጠኸው የአባቴ የስምዖን አምላክ ሆይ፥ አንተ እንዲህ አይደለም አልህ፤ እነርሱ ግን አደረጉት። |