በእርሻ ውስጥ ነዶ ከሚያስሩ ሰዎች ቆሞ ሳለ ራሱን ንዳድ መታው፥ ታምሞ ተኛ፤ በገዛ ሀገሩ በቤቱሊያ ከተማ ሞተ፤ በዶታንና በባላሞን መካከል በሚገኝ እርሻ ውስጥ ከአባቶቹ ጋር ቀበሩት።
ነዶ ከሚያስሩ ሰዎች ጋራ በእርሻ ውሏልና ራሱን ምች መታው፤ ታምሞ ተኛ፤ በሀገሩ በቤጤልዋም ሞተ፤ እንደ አባቶቹም በሀገሩ በዶታይምና በበላሞን ባለ ቦታ ቀበሩት።