የወንድሞቻችን መገደልና የምድሪቱ መያዝ፥ የርስታችንም መጥፋት ባርያዎች በምንሆንበት ሁሉ በአሕዛብ መካከል በራሳችን ላይ ይመለሳል፤ በሚገዙን ፊትም እንቅፋትና ስድብ እንሆናለን።
የወንድሞቻችን መገደል፥ የሀገራችንም መዘረፍ፥ የርስታችንም ምድረ በዳ መሆን በሚገዙን አሕዛብ ዘንድ በእኛ ላይ ይመለሳል፤ ገንዘብ በሚያደርጉን ፊትም በዚያ የተሰነካከልንና መገዳደሪያ እንሆናለን።