ከቤቱሊያ አጠገብ ባለው ሸለቆ ከምንጩ ዳር ሰፈሩ፤ በስፋት ከዶታን እስከ ቤልባይም በርዝመት ደግሞ ከቤቱሊያ በኤስድራሎን ፊት ለፊት እስከሚገኘው እስከ ሳያሞን ድረስ ተስፋፉ።
በቤጤልዋ አጠገብ፥ በአውሎን በውኃው ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ፤ የሰፈራቸውም አቆልቋዩ እስከ ዶታይምና ቤጤልዋ ድረስ፥ ወርዱም በአሴዴራሎም አንጻር ከቤጤልዋ እስከ ቅያሞስ ደረሰ።