በዚያን ቀን ኃያላን ሰዎቻቸው በሙሉ ከጦር ሰፈራቸው ወጡ፥ ተዋጊዎቹ ቁጥራቸው መቶ ሰባ ሺህ እግረኛና ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሰኛ ጦር ነበረ ይህም ጓዝ የሚጠብቁና እጅግ ብዙ እግረኛ ሰዎች ሳይቆጠሩ ነው።
በዚያም ቀን ጽኑዓን አርበኞች የሆኑ ኀይለኞች ሰዎች ሁሉ ወረዱ፤ እነዚያም ጓዝ ከሚጠብቁ ካልከበቡ ከብዙ አርበኞች ሰዎች በቀር መቶ ሰባ ሺህ እግረኞችና ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሰኞች ነበሩ።