መጽሐፈ ዮዲት 15:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡም ሁሉ የጦር ሰፈሩን ሠላሳ ቀን ያህል ዘረፉ፥ ለዮዲትም የሆሎፎርኒስን ድንኳንና የብሩን ሣህን ሁሉ፥ አልጋዎቹንና ጎድጓዳ ሣህኖቹን፥ የቤት ዕቃዎቹን ሁሉ ሰጧት፤ እርሷም ወስዳ በበቅሎዋ ላይ ጫነች፤ ሠረገላዎችዋንም አዘጋጀትና እዚያ ላይ ጫነችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቡም ሠላሳ ቀን ሰፈራቸውን በረበሩ፤ ለዮዲትም የሆሎፎርኒስን ድንኳንና የብሩን ዕቃ ሁሉ፥ ዙፋኑንና ያለውንም ገንዘብ ሁሉ ሰጧት፤ እርሷም ወስዳ በበቅሎዋ ጫነች፤ ሠረገላዎችዋንም ነድታ ከእርሷ ጋር ይዛ ገባች። |