መጽሐፈ ዮዲት 13:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዑዚያም እንዲህ አላት፦ “ልጄ ሆይ፥ በምድር ካሉ ሴቶች ሁሉ ይልቅ በልዑል እግዚአብሔር የተባረክሽ ነሽ፤ ሰማይንና ምድርን የፈጠረ የጠላቶቻችን አለቃ አንገት ለመቁረጥ የመራሽ ጌታ እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዖዝያንም እንዲህ አላት፥ “በዚህ ዓለም ከሚኖሩ ሴቶች ይልቅ አንቺ ልጄ፥ ልዑል እግዚአብሔር የባረከሽ ነሽ። ሰማይንና ምድርን የፈጠረ፥ የጠላቶቻችንን አለቃ ቸብቸቦ ትቈርጪ ዘንድ የረዳሽ እግዚአብሔር አምላክም ቡሩክ ነው። |