መሳፍንት 9:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህ ካልሆነ ግን እሳት ከአቤሜሌክ ትውጣና እናንተን፥ የሴኬምንና የቤትሚሎን ነዋሪዎች ትብላ፤ እንዲሁም እሳት ከእናንተ፥ ከሴኬምና ከቤትሚሎን ነዋሪዎች ትውጣና አቤሜሌክን ትብላ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ ካልሆነ ግን እሳት ከአቢሜሌክ ትውጣና እናንተን፣ የሴኬምንና የቤት ሚሎን ነዋሪዎች ትብላ፤ እንዲሁም እሳት ከእናንተ፣ ከሴኬምና ከቤት ሚሎን ገዦች ትውጣና አቢሜሌክን ትብላ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ ካልሆነ ግን ከአቤሜሌክ እሳት ወጥቶ የሴኬምንና የቤትሚሎንን ሰዎች ይብላ፤ እንዲሁም ከሴኬምና ከቤትሚሎ እሳት ወጥቶ አቤሜሌክን ይብላ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህ ባይሆን ግን ከአቤሜሌክ እሳት ትውጣ፤ የሰቂማንም ሰዎች፥ የመሐሎንንም ቤት ትብላ፤ ያም ባይሆን ከሰቂማ ሰዎች ከመሐሎንም ቤት እሳት ትውጣ፤ አቤሜሌክንም ትብላው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህ ባይሆን ግን ከአቤሜሌክ እሳት ይውጣ፥ የሴኬምንም ሰዎች ቤትሚሎንም ይብላ፥ ከሴኬምም ሰዎች ከቤትሚሎም እሳት ይውጣ፥ አቤሜሌክንም ይብላ። |
የሦስት መቶው ቀንደ መለከት ድምፅ እንደተሰማም ጌታ በሰፈሩ ውስጥ ያለው ሰው አንዱ በሌላው ላይ ሰይፉን እንዲመዝበት አደረገ፤ ሠራዊቱ በጽሬራ አቅጣጫ እስከ ቤትሺጣ፥ ከዚያም አልፈው በጠባት አጠገብ እስካለው እስከ አቤልመሖላ ድንበር ድረስ ሸሽተው ሄዱ።
የእሾኽ ቊጥቋጦውም ዛፎቹን፥ “በእርግጥ ቀብታችሁ በላያችሁ የምታነግሡኝ ከሆነ መጥታችሁ በጥላዬ ሥር ተጠለሉ፤ ይህን ባታደርጉ ግን እሳት ከእሾ ቊጥቋጦው ይነሣ፤ የሊባኖስንም ዝግባዎች ይብላ” አላቸው።
እንግዲህ ዛሬ በይሩበኣልና በቤተሰቡ ላይ ያደረጋችሁት በእውነትና በቅንነት ከሆነ እናንተ በአቤሜሌክ ደስ ይበላችሁ፤ እርሱም በእናንተ ደስ ይበለው
ከዚያም አቤሜሌክና አብረውት የነበሩ ምድቦች ቦታ ለመያዝ በፍጥነት ወደ ከተማይቱ መግቢያ በሚሮጡበት ጊዜ፥ ሌሎቹ ሁለት ምድቦች ደግሞ እየሮጡ ሄደው በዕርሻው ያሉትን ሁሉ ፈጇቸው።