የኤፍሬም ሰዎች ኃይላቸውን አሰባስበው ወደ ጻፎን በመሻገር ዮፍታሔን፥ “አሞናውያንን ለመውጋት ስትወጣ አብረንህ እንድንሄድ ያልጠራኸን ለምንድን ነው? ቤትህን በላይህ ላይ እናቃጥለዋለን አሉት።”
መሳፍንት 12:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮፍታሔም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “እኔና ሕዝቤ ከአሞናውያን ጋር ከፍተኛ ትግል ገጥመን በነበረበት ጊዜ ጠርቼያችሁ ከእጃቸው አላዳናችሁኝም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮፍታሔም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “እኔና ሕዝቤ ከአሞናውያን ጋራ ከፍተኛ ትግል ገጥመን በነበረበት ጊዜ ጠርቼያችሁ ከእጃቸው አላዳናችሁኝም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮፍታሔም እንዲህ አላቸው፤ “እኔና ሕዝቤ ከዐሞናውያን ጋር በብርቱ ተጣልተን በነበረበት ጊዜ እናንተን ጠርቼአችሁ ነበር፤ ነገር ግን ከእነርሱ ጥቃት አላዳናችሁኝም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮፍታሔም፥ “እኔና ሕዝቤ የተገፋን ነን፤ የአሞን ልጆችም በጽኑዕ አሠቃዩን፤ በጠራናችሁም ጊዜ ከእጃቸው አላዳናችሁንም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮፍታሔም፦ ከአሞን ልጆች ጋር ለእኔና ለሕዝቤ ጽኑ ጠብ ነበረን፥ በጠራኋችሁም ጊዜ ከእጃቸው አላዳናችሁኝም። |
የኤፍሬም ሰዎች ኃይላቸውን አሰባስበው ወደ ጻፎን በመሻገር ዮፍታሔን፥ “አሞናውያንን ለመውጋት ስትወጣ አብረንህ እንድንሄድ ያልጠራኸን ለምንድን ነው? ቤትህን በላይህ ላይ እናቃጥለዋለን አሉት።”
እኔም እንደማትረዱኝ በተረዳሁ ጊዜ በሕይወቴ ቈርጬ አሞናውያንን ለመውጋት ተሻገርሁ፤ ጌታም ድሉን ሰጠኝ፤ ታዲያ ዛሬ እኔን ለመውጋት የመጣችሁት ለምንድን ነው?”