በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር፥ ከሸለቆውም ውስጥ ካለችው ከተማ ጀምረን እስከ ገለዓድ ድረስ፥ የትኛይቱም ከተማ አልተቋቋመችንም፤ ጌታ አምላካችን ሁሉን አሳልፎ ሰጠን።
መሳፍንት 11:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአርኖን እስከ ያቦቅ፥ ከምድረ በዳው እስከ ዮርዳኖስ ድረስ ያለውን ምድር በሙሉ ወረሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከአርኖን እስከ ያቦቅ፣ ከምድረ በዳው እስከ ዮርዳኖስ ድረስ ያለውን የአሞራውያንን ድንበር በሙሉ ወረሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በደቡብ ከአርኖን ወንዝ አንሥቶ በሰሜን እስከ ያቦቅ ወንዝ ድረስ፥ እንዲሁም በምሥራቅ ከበረሓው አንሥቶ በምዕራብ እስከ ዮርዳኖስ ወንዝ ድረስ መላውን የአሞራውያን ግዛት ያዙ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአርኖንም እስከ ያቦቅ ድረስ፥ ከምድረ በዳውም እስከ ዮርዳኖስ ድረስ የአሞሬዎናውያንን አውራጃ ሁሉ ወረሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአርኖንም እስከ ያቦቅ ድረስ ከምድረ በዳውም እስከ ዮርዳኖስ ድረስ የአሞራውያንን ምድር ሁሉ ወረሱ። |
በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር፥ ከሸለቆውም ውስጥ ካለችው ከተማ ጀምረን እስከ ገለዓድ ድረስ፥ የትኛይቱም ከተማ አልተቋቋመችንም፤ ጌታ አምላካችን ሁሉን አሳልፎ ሰጠን።
ብቻ ጌታ አምላካችን ወደ ከለከለን፥ ወደ አሞን ልጆች ምድር በያቦቅም ወንዝ አጠገብ ወዳለው ስፍራ ሁሉ በተራራማውም አገር ወዳሉት ከተሞች አልቀረብንም።