የእነዚህም ዐሥራ ሁለት የክፍላተ ሀገር ገዢዎችና የሚያስተዳድሩአቸውም ግዛቶች ስም ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው፥ ቤንሑር፦ ኰረብታማ የሆነችው የኤፍሬም አገር ገዢ፤
ኢያሱ 19:50 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኤፍሬም ተራራማ አገር ያለችውን እንዲሰጡት የጠየቃቸውን ተምናሴራ የምትባለውን ከተማ እንደ ጌታ ትእዛዝ ሰጡት፤ ከተማም ሠርቶ ተቀመጠባት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ባዘዘውም መሠረት በኰረብታማው የኤፍሬም ምድር የምትገኘውን ተምናሴራ የምትባለውን የፈለጋትን ከተማ ሰጡት፤ እርሱም ከተማዪቱን ሠራ፤ መኖሪያውም አደረጋት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም ባዘዘው መሠረት በኮረብታማው በኤፍሬም አገር እንዲሰጡት የጠየቃቸውን ቲምናትሴራሕ ተብላ የምትጠራውን ከተማ ሰጡት፤ ያቺንም ከተማ እንደገና ሠርቶ መኖሪያው አደረጋት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኤፍሬም ተራራማ ሀገር ያለችውን ተምናሴራ የምትባለውን የፈለጋትን ከተማ ሰጡት፤ ከተማም ሠርቶ ተቀመጠባት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኤፍሬም ተራራማ አገር ያለችውን ተምናሴራ የምትባለውን የፈለጋትን ከተማ እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ ሰጡት፥ ከተማም ሠርቶ ተቀመጠባት። |
የእነዚህም ዐሥራ ሁለት የክፍላተ ሀገር ገዢዎችና የሚያስተዳድሩአቸውም ግዛቶች ስም ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው፥ ቤንሑር፦ ኰረብታማ የሆነችው የኤፍሬም አገር ገዢ፤