ኢያሱ 18:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንበሩም ወደ ቤትሖግላ ወደ ሰሜን ወገን አለፈ፤ የድንበሩም መጨረሻ በዮርዳኖስ መጨረሻ በደቡብ በኩል ባለው በጨው ባሕር ልሳን አጠገብ ነበረ፤ ይህ የደቡቡ ዳርቻ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሰሜናዊውን የቤትሖግላንን ተረተር ዐልፎ ይሄድና በስተ ደቡብ የዮርዳኖስ ወንዝ እስከሚገባበት እስከ ጨው ባሕር ወሽመጥ ይዘልቃል፤ ይህም ደቡባዊ ድንበሩ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ድንበሩ በቤትሆግላ ጐን ያልፋል፤ ከጨው ባሕር በስተሰሜን እስከ ዮርዳኖስ ወንዝ ደቡብ ድረስ ይሄዳል። ይህም የደቡቡ ድንበር ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የድንበራቸውም ፍጻሜ በሰሜን በኩል ወደ ጨው ባሕር ልሳን ይደርሳል፤ በደቡብም በኩል ድንበራቸው ዮርዳኖስ ነው። ይህም በደቡብ በኩል ያለው ድንበር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንበሩም ወደ ቤትሖግላ ወደ ሰሜን ወገን አለፈ፥ መውጫውም በዮርዳኖስ መጨረሻ በደቡብ በኩል ባለው በጨው ባሕር ልሳን አጠገብ ነበረ፥ ይህ የደቡቡ ዳርቻ ነበረ። |
ጌታ በሚጋረፍም ነፋስ የግብጽን ባሕረ ሰላጤ ያደርቃል፤ እጁን በኤፍራጥስ ወንዝ ላይ ይዘረጋል፤ ሰባት ታናናሽ ጅረትም አድርጎ ይለያየዋል፤ ስለዚህ ሰዎች ከነጫማቸው መሻገር ይችላሉ።
የደቡቡ ወገን ከጺን ምድረ በዳ ተነሥቶ የኤዶምያስን ዳርቻ እያዋሰነ የሚያልፈው ይሆናል፤ የደቡቡም ድንበራችሁ ከጨው ባሕር ዳር በምሥራቅ በኩል ይጀምራል፤
ዓረባንም፥ ከዮርዳኖስ ጋር እንደ ወሰን፥ ከኪኔሬት እስከ ዓረባ ባሕር ድረስ፥ የጨው ባሕር፥ ከፈስጋ ተራራ በታች ወደ ምሥራቅ ያለውን ያካትታል።
በምሥራቅም በኩል ያለውን ዓረባ እስከ ኪኔሬት ባሕር ድረስ፥ በቤትየሺሞት መንገድ አጠገብ እስካለው እስከ ዓረባ ባሕር እስከ ጨው ባሕር ድረስ፥ በደቡብም በኩል ከፈስጋ ተራራ አፋፍ በታች ያለውን ምድር ነበር፤
ከላይ የሚወርደው ውኃ ቆመ፤ በጻርታን አጠገብ ባለችው አዳም በምትባል ከተማ በሩቅ ቆሞ በአንድ ክምር ተነሣ፤ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚወርደው ውኃ ፈጽሞ ተቋረጠ፤ ሕዝቡም በኢያሪኮ ፊት ለፊት ተሻገሩ።