ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች ሁሉ፥ በኪሩቤል ላይ በተቀመጠ በሠራዊት ጌታ ስም የተጠራውን የእግዚአብሔርን ታቦት ከዚያ ለማምጣት በይሁዳ ወዳለችው በዓል ሄዱ።
ኢያሱ 18:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንበሩም ወደ ምዕራብ ሄደ፥ በቤትሖሮንም ፊት ለፊት ካለው ተራራ ወደ ደቡብ ዞረ፤ መጨረሻውም ቂርያት-ይዓሪም በምትባል በቂርያትበኣል በይሁዳ ልጆች ከተማ ነበረ፤ ይህ የምዕራቡ ዳርቻ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በስተ ደቡብ ያለው ድንበር ከቤትሖሮን ትይዩ ካለው ኰረብታ ተነሥቶ፣ በምዕራብ በኩል ወደ ደቡብ በመታጠፍ፣ የይሁዳ ነገድ ከተማ ወደሆነችው ወደ ቂርያትበኣል ማለት ወደ ቂርያትይዓይሪም ያልፋል፤ ይህ እንግዲህ በምዕራብ በኩል ያለው ድንበር ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይኸው ድንበር በሌላም አቅጣጫ ከዚህ ተራራ በስተ ምዕራብ ወደ ደቡብ በመታጠፍ የይሁዳ ነገድ ይዞታ ወደ ሆነችው ከተማ ወደ ቂርያትባዓል ወይም ቂርያትይዓሪም ያልፋል፤ ይህም በምዕራብ በኩል የሚገኘው ድንበር ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንበሩም ወደ ባሕር ሄደ፤ በቤቶሮንም ፊት ለፊት ካለው ተራራ ወደ አዜብ ዞረ፤ መውጫውም ቂርያታርም በምትባል በይሁዳ ልጆች ከተማ በቂርያትበኣል ነበረ፤ ይህ በባሕር በኩል ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንበሩም ወደ ምዕራብ ሄደ፥ በቤትሖሮንም ፊት ለፊት ካለው ተራራ ወደ ደቡብ ዞረ፥ መውጫውም ቂርያትይዓሪም በምትባል በይሁዳ ልጆች ከተማ በቂርያትበኣል ነበረ፥ ይህ የምዕራቡ ዳርቻ ነበረ። |
ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች ሁሉ፥ በኪሩቤል ላይ በተቀመጠ በሠራዊት ጌታ ስም የተጠራውን የእግዚአብሔርን ታቦት ከዚያ ለማምጣት በይሁዳ ወዳለችው በዓል ሄዱ።
ድንበሩም ከተራራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ደረሰ፥ ከዚያም ተነስቶ ወደ ዔፍሮን ተራራ ከተሞች ወጣ፤ ቂርያት-ይዓሪም ወደምትባል ወደ በኣላ ታጠፈ፤
ድንበሩም ከዚያ በደቡብ በኩል በሎዛ አቅጣጫ ቤቴል ወደምትባል ወደ ሎዛ ወገን አለፈ፤ ድንበሩም በታችኛው ቤትሖሮን በደቡብ በኩል ባለው ተራራ ወደ አጣሮትአዳር ወረደ።