አባቱም እንዲህ ሲል እንቢታውን ገለጸ፦ “አውቄአለሁ ልጄ ሆይ፥ አውቄአለሁ፥ ይህም ደግሞ ሕዝብ ይሆናል ታላቅም ይሆናል፥ ነገር ግን ታናሽ ወንድሙ ከእርሱ ይበልጣል፥ ዘሩም የአሕዛብ ሙላት ይሆናል።”
ኢያሱ 17:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዮሴፍ ልጆች ነገድ ኢያሱን እንዲህ አለው፦ “እኔ ብዙ ሕዝብ ስለ ሆንኩ እስከ አሁንም ጌታ ስለ ባረከኝ ለምን አንድ ድርሻ አንድም ዕጣ ብቻ ርስት አድርገህ ሰጠኸኝ?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዮሴፍ ዘሮች ኢያሱን፣ “ቍጥራችን ብዙ ነው፤ እግዚአብሔርም አብዝቶ ባርኮናል፤ ታዲያ እንዴት ርስታችን አንድ ዕጣና አንድ ድርሻ ብቻ ሆነ?” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዮሴፍ ነገድ ወደ ኢያሱ ቀርበው “እግዚአብሔር ባርኮን ለበዛነው ለእኛ እንዴት አንድ ዕጣ ብቻ ሰጠኸን?” ብለው ጠየቁት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዮሴፍም ልጆች ኢያሱን፥ “እኛ ብዙ ሕዝብ ስንሆን እስከ አሁንም እግዚአብሔር ስለ ባረከን ለምን አንድ ክፍል፥ አንድም ዕጣ ብቻ ርስት አድርገህ ሰጠኸን?” ብለው ወቀሱት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዮሴፍ ልጆች ኢያሱን፦ እኔ ብዙ ሕዝብ ስለ ሆንሁ እስከ አሁንም እግዚአብሔር ስለ ባረከኝ ለምን አንድ ክፍል አንድም ዕጣ ብቻ ርስት አድርገህ ሰጠኸኝ? አሉት። |
አባቱም እንዲህ ሲል እንቢታውን ገለጸ፦ “አውቄአለሁ ልጄ ሆይ፥ አውቄአለሁ፥ ይህም ደግሞ ሕዝብ ይሆናል ታላቅም ይሆናል፥ ነገር ግን ታናሽ ወንድሙ ከእርሱ ይበልጣል፥ ዘሩም የአሕዛብ ሙላት ይሆናል።”
ስለዚህ በዚያን ቀን እንዲህ ሲል ባረካቸው፤ “እስራኤላውያን በሚመርቁበት ጊዜ የእናንተን ስም በማስታወስ፥ ‘እግዚአብሔር እንደ ኤፍሬምና እንደ ምናሴ ያድርጋችሁ’ ይላሉ።”
በየወገናቸው ለብዙዎቹ እንደ ብዛታቸው፥ ለጥቂቶቹም እንደ ጥቂትነታቸው መጠን ርስትን ትሰጣቸዋለህ። ለሁሉ እንደ ቁጥራቸው መጠን ርስታቸው ይሰጣቸዋል።
ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ “ብዙ ሕዝብስ ከሆንህ ተራራማውም የኤፍሬም አገር ጠብቦህ እንደሆነ ወደ ዱር ወጥተህ በፌርዛውያንና በራፋይም ምድር ለአንተ ስፍራ መንጥር።”