“ትካዜዬ ምነው በተመዘነ! መከራዬም በሚዛን ላይ ምነው በተቀመጠ!
“ምነው ሐዘኔ በተመዘነ! መከራዬም ሚዛን ላይ በተቀመጠ!
“ትካዜዬ ምነው በተመዘነ ኖሮ! መከራዬም ሁሉ ምነው በሚዛን ላይ በታየ ኖሮ!
“ከእናንተ አንዱ መቅሠፍቴን ምነው በመዘነ ኖሮ! መከራዬንም በአንድነት ምነው በሚዛን ላይ ባኖረው ኖሮ!
ትካዜዬ ምነው በተመዘነ ኖሮ! መከራዬም ሁሉ ምነው በሚዛን ላይ በተደረገ ኖሮ!
“ዛሬም ደግሞ የኀዘን እንጉርጉሮዬ ገና መራራ ነው፥ በመቃተት ብጮኽም እጁ በእኔ ላይ እንደ ከበደች ናት።
አሁን ግን በአንተ ላይ መጥቷል፥ አንተም ደከምህ፥ ደርሶብሃል፥ አንተም ተረበሽህ።
ኢዮብም መለሰ፤ እንዲህም አለ፦
የራሱን ኀዘን ልብ ያውቃል፥ ከደስታውም ጋር ሌላ ሰው አይገናኝም።