ኢዮብ 42:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮብም ስለ ወዳጆቹ ሲጸልይ ጌታ ምርኮውን መለሰለት፥ ጌታ ቀድሞ በነበረው ፋንታ በሁለት እጥፍ አሳድጎ ለኢዮብ ሰጠው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮብ ለወዳጆቹ ከጸለየ በኋላ፣ እግዚአብሔር እንደ ገና አበለጸገው፤ ቀድሞ በነበረው ፈንታ ዕጥፍ አድርጎ ሰጠው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮብ ለሦስቱ ወዳጆቹ ከጸለየ በኋላ እግዚአብሔር እንደገና እንዲበለጽግ አደረገው፤ ዱሮ ከነበረውም ይበልጥ እጥፍ አድርጎ ሰጠው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ኢዮብን አዳነው። ኢዮብም ስለ ወዳጆቹ ጸለየ፥ እግዚአብሔርም ኀጢአታቸውን ተወላቸው፤ እግዚአብሔርም ቀድሞ በነበረው ገንዘቡ ሁሉ ፋንታ ሁለት እጥፍ ከዚያም በላይ አድርጎ ለኢዮብ ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮብም ስለ ወዳጆቹ በጸለየ ጊዜ እግዚአብሔርም ምርኮውን መለሰለት፥ እግዚአብሔር ቀድሞ በነበረው ፋንታ ሁለት እጥፍ አድርጎ ለኢዮብ ሰጠው። |
አሜስያስም የእግዚአብሔርን ሰው እንዲህ አለው፦ “ለእስራኤል ሠራዊት የሰጠሁት መቶ መክሊት ምን ይሆን?” የጌታም ሰው እንዲህ ብሎ መለሰለት፦ “ጌታ ከዚህ አብልጦ ሊሰጥህ ይችላል።”
ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመሎች፥ አምስት መቶ ጥማድ በሬዎች፥ አምስት መቶ እንስት አህዮችና እጅግ ብዙም አገልጋዮች ነበሩት። ያም ሰው በምሥራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ታላቅ ነበረ።
ለኢየሩሳሌም ልብ ተናገሩ፤ የተቀጠረችበት ወራት እንደ ተፈጸመ፥ ኃጢአትዋም እንደ ተሰረየ፥ ከጌታም እጅ ስለ ኃጢአትዋ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀበለች ወደ እርሷ ጩኹ።
በኀፍረታችሁ ፈንታ ሁለት እጥፍ ይሆንላችኋል፤ በውርደታችሁም ፋንታ ዕድል ፋንታችሁ ደስ ይለዋል፤ ስለዚህ የምድራቸውን ሁለት እጥፍ ይገዛሉ፥ የዘለዓለምም ደስታ ይሆንላቸዋል።
ተንበርክኮም “ጌታ ሆይ! ይህን ኃጢአት አትቁጠርባቸው፤” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህንም ብሎ አንቀላፋ። ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር።
ባለጸጋ እንድትሆን ኃይልና ብርታት የሰጠህ ጌታ አምላክህ መሆኑን አስታውስ፤ ይህም ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ ከቀድሞ አባቶችህ ጋር በመሐላ የገባውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ ነው።
በትዕግሥት የጸኑትን የተባረኩ አድርገን እንደምንቈጥር ታውቃላችሁ፤ ኢዮብ እንዴት ታግሦ እንደ ጸና ሰምታችኋል፤ ጌታም በመጨረሻ ያደረገለትን አይታችኋል። ጌታ እጅግ ርኅሩኅና መሓሪ ነው።
ወደ ልዑላንም ደረጃ ከፍ ሊያደርጋቸው፥ የክብርንም ዙፋን ሊያወርሳቸው፥ እርሱ ድኾችን ከትቢያ፥ ምስኪኖችንም ከዐመድ ላይ ያነሣል፤ የምድር መሠረቶች የጌታ ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አኖረ።