ኤልያስ አንድ ቀን ሙሉ በበረሓ ተጓዘ፤ ከዚህ በኋላ ጉዞውን ቆም አድርጎ፥ በአንድ የክትክታ ዛፍ ጥላ ሥር ተቀመጠ፤ ሞቱንም በመመኘት “ጌታ ሆይ! አሁንስ ይብቃኝ፤ ከቀድሞ አባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ!” ሲል ጸለየ።
ኢዮብ 10:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሕይወቴ ሰለቸኝ፥ የኀዘን እንጉርጉሮዬን እለቅቀዋለሁ፥ በነፍሴም ምሬት እናገራለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሕይወቴን እጅግ ጠላሁ፤ ስለዚህም ማጕረምረሜን ያለ ገደብ እለቅቃለሁ፤ በነፍሴም ምሬት እናገራለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “መኖር ሰልችቶኛል፤ የማሳልፈውን መራራ ሕይወት በግልጽ አሰማለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ነፍሴ ስለ ተጨነቀች ቃሌን በእንጕርጕሮ አሰማለሁ፤ ነፍሴም እየተጨነቀች በምሬት እናገራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነፍሴ ሕይወቴን ሰለቸቻት፥ የኀዘን እንጕርጕሮዬን እለቅቀዋለሁ፥ በነፍሴም ምሬት እናገራለሁ። |
ኤልያስ አንድ ቀን ሙሉ በበረሓ ተጓዘ፤ ከዚህ በኋላ ጉዞውን ቆም አድርጎ፥ በአንድ የክትክታ ዛፍ ጥላ ሥር ተቀመጠ፤ ሞቱንም በመመኘት “ጌታ ሆይ! አሁንስ ይብቃኝ፤ ከቀድሞ አባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ!” ሲል ጸለየ።
ፀሐይም በወጣ ጊዜ እግዚአብሔር የሚያቃጥል የምሥራቅ ነፋስ አዘጋጀ፥ ዮናስ ራሱን እስኪስት ድረስ ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለነፍሱም ሞትን ለመነና “ከሕይወት ሞት ይሻላል” አለ።