ኤርምያስ 8:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “መከሩ አልፎአል፥ በጋው ተፈጽሟል፥ እኛም አልዳንም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “መከሩ ዐለፈ፤ በጋው አበቃ፤ እኛም አልዳንም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡም “እነሆ የመከር ወራት አለፈ፤ በጋውም ተፈጸመ፤ እኛ ግን አልዳንም!” በማለት ይጮኻሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መከሩ አልፎአል፤ በጋውም ዐልቋል፤ እኛም አልዳንንም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መከሩ አልፎአል፥ በጋው ሄዶአል፥ እኛም አልዳንነም። |
እነሆ፦ “ጌታ በጽዮን የለምን? ወይስ ንጉሥዋ በእርሷ መካከል የለምን?” የሚል የወገኔ ሴት ልጅ ጩኸት ድምፅ ከሩቅ አገር ተሰማ። “በተቀረጹ ምስሎቻቸውና በባዕድ ከንቱነትስ ያስቈጡኝ ስለ ምንድነው?”
ባለቤቱ ተነሥቶ በሩን ከቈለፈ በኋላ፥ እናንተ በውጭ ቆማችሁ ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! ክፈትልን’ እያላችሁ በሩን ማንኳኳት ትጀምራላችሁ፤ እርሱም መልሶ ‘ከየት እንደ ሆናችሁ አላውቅም’ ይላችኋል።
አንቺንም በአንቺም ውስጥ የሚኖሩትን ልጆችሽን በምድር ላይ ይጨፈልቃሉ፤ በአንቺ ውስጥም በድንጋይ ላይ የሚኖር ድንጋይ አያስቀሩም፤ የተጐብኘሽበትን ዘመን አላወቅሽምና።”