ንጉሡ ሴዴቅያስ ልኮ አስመጣው፥ ንጉሡም በቤቱ፦ “በውኑ ከጌታ ዘንድ የሆነ ቃል አለን?” ብሎ በድብቅ ጠየቀው። ኤርምያስም፦ “አዎን አለ” ብሎ መለሰ። ከዚያም በኋላ፦ “በባቢሎን ንጉሥ እጅ ተላልፈህ ትሰጣለህ” አለ።
ኤርምያስ 38:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴዴቅያስም ኤርምያስን እንዲህ አለው፦ “እነዚህንም ቃላት ማንም አይወቅ፥ አንተም አትሞትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴዴቅያስም ኤርምያስን እንዲህ አለው፤ “ስለዚህ ስለ ተነጋገርነው ነገር ማንም አይወቅ፤ አለዚያ ትሞታለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴዴቅያስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እንዳትሞት ይህን የተነጋገርነውን ነገር ማንም አይወቅ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴዴቅያስም ኤርምያስን እንዲህ አለው፥ “ይህን ቃል ማንም አይወቅ፥ አንተም አትሞትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴዴቅያስም ኤርምያስን እንዲህ አለው፦ ይህም ቃል ማንም አይወቅ፥ አንተም አትሞትም። |
ንጉሡ ሴዴቅያስ ልኮ አስመጣው፥ ንጉሡም በቤቱ፦ “በውኑ ከጌታ ዘንድ የሆነ ቃል አለን?” ብሎ በድብቅ ጠየቀው። ኤርምያስም፦ “አዎን አለ” ብሎ መለሰ። ከዚያም በኋላ፦ “በባቢሎን ንጉሥ እጅ ተላልፈህ ትሰጣለህ” አለ።
ሚስቶችህንና ልጆችህንም ሁሉ ወደ ከለዳውያን ያወጣሉ፤ አንተም በባቢሎን ንጉሥ እጅ ትያዛለህ እንጂ ከእጃቸው አታመልጥም፤ ይህችም ከተማ በእሳት ትቃጠላለች።”
አለቆቹ ግን እኔ ከአንተ ጋር እንደተነጋገርሁ ቢሰሙ፥ ወደ አንተም መጥተው፦ ‘ለንጉሡ ያልኸው ምንድነው? ንገረን አትሸሽገንም፥ እኛም አንገድልህም፤ ንጉሡስ ለአንተ ምን አለህ?’ ንገረን ቢሉህ፥