ኤርምያስ 38:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤሜሌክም ከእርሱ ጋር ሰዎችን ይዞ ሄደ፥ ከቤተ መዛግብቱም በታች ወደነበረው ወደ ንጉሥ ቤት ገባ፥ ከዚያም አሮጌ ጨርቅና እላቂ ልብስ ወሰደ፥ ወደ ኤርምያስም ወደ ጉድጓድ ውስጥ በገመድ አወረደው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አቢሜሌክም ሰዎቹን ይዞ በቤተ መንግሥቱ ግምጃ ቤት ሥር ወዳለው ክፍል ሄደ፤ ያረጀ ጨርቅና ያለቀ ልብስ ከዚያ ወስዶ ወደ ኤርምያስ ወደ ጕድጓዱ ውስጥ በገመድ አወረደለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም አቤሜሌክ ሰዎቹን አስከትሎ ሄደ፤ ወደ ቤተ መንግሥቱ ዕቃ ግምጃ ቤትም ገብቶ ወፍራም ጨርቅና አሮጌ ልብስ አገኘ፤ እርሱንም በገመድ አስሮ ሰደደልኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤሜሌክም ከእርሱ ጋር ሰዎችን ይዞ ሄደ፤ ከቤተ መዛግብቱም በታች ወደ ነበረው ወደ ንጉሥ ቤት ገባ፤ ከዚያም ዕላቂ ጨርቅና አሮጌ ገመድ ወሰደ፥ ወደ ኤርምያስም ወደ ጕድጓዱ ውስጥ በገመድ አወረደው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤሜሌክም ከእርሱ ጋር ሰዎችን ይዞ ሄደ፥ ከቤተ መዛግብቱም በታች ወደ ነበረው ወደ ንጉሥ ቤት ገባ፥ ከዚያም አሮጌ ጨርቅና እላቂ ልብስ ወሰደ፥ ወደ ኤርምያስም ወደ ጉድጓድ ውስጥ በገመድ አወረደው። |
ኢትዮጵያዊውም አቤሜሌክ ኤርምያስን፦ “ይህን አሮጌ ጨርቅና እላቂውን ልብስ በብብትህ ከገመዱ በታች አድርግ” አለው፤ ኤርምያስም እንዲሁ አደረገ።
ኤርምያስንም ወሰዱት፤ በእስር ቤቱም አደባባይ ወደነበረው ወደ ንጉሡ ልጅ ወደ መልክያ ጉድጓድ ውስጥ ኤርምያስን በገመድ አውርደው ጣሉት። በጉድጓድም ውስጥ ጭቃ እንጂ ውኃ አልነበረበትም፤ ኤርምያስም ወደ ጭቃው ውስጥ ገባ።