ኢሳይያስ 14:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡ አካዝ በሞተበት ዘመን ይህ ሸክም ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡ አካዝ በሞተበት ዓመት እንዲህ የሚል ንግር መጣ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ አካዝ በሞተበት ዓመት የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡ አካዝ በሞተበት ዓመት ይህ ነገር ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡ አካዝ በሞተበት ዘመን ይህ ሸክም ሆነ። |
አካዝም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ በከተማይቱም በኢየሩሳሌም ቀበሩት፤ ነገር ግን ወደ እስራኤል ነገሥታት መቃብር አላገቡትም፤ ልጁም ሕዝቅያስ በእርሱ ፋንታ ነገሠ።
አስቀሎና አይታ ትፈራለች፤ ጋዛ በሥጋት ትታመማለች፤ እንዲሁም አቃሮን፥ ተስፋዋ ይመነምናል። ንጉሡም ከጋዛ ይጠፋል፥ በአስቀሎናም የሚኖር አይገኝም።