ዘፍጥረት 9:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኖኅም ከወይን ጠጁ ስካር ሲነቃ፥ ታናሽ ልጁ ያደረገበትን አወቀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኖኅ ከወይን ጠጁ ስካር ሲነቃ፣ ታናሽ ልጁ ያደረገበትን ዐወቀ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኖኅ ስካሩ አልፎለት ሲነቃ፥ ትንሹ ልጁ ያደረገበትን ዐወቀ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኖኅም ከወይኑ ስካር በነቃ ጊዜ፥ ታናሹ ልጁ ያደረገበትን ዐወቀ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኖኅም ከወይን ጠጅ ስካር ነቃ፥ ታናሹ ልጁ ያደረገበትንም አወቀ። |
ሴምና ያፌትም ልብስ በትከሻቸው ላይ አደረጉ፥ የኋሊትም ሄደው የአባታቸውን ዕራቁትነት አለበሱ፤ ፊታቸውም ወደ ኋላ ነበረ፥ የአባታቸውንም ዕራቁትነት አላዩም።