ዘፍጥረት 9:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድር በደመና በምትሸፈንበት ቀስቲቱም በደመናው በምትታይበት ጊዜ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደመናን በምድር ላይ በጋረድሁና ቀስቴም በደመና ላይ በሚታይበት ጊዜ ሁሉ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰማይን በደመና በምሸፍንበትና ቀስትም በደመና ላይ በሚታይበት ጊዜ ሁሉ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድር ላይ ደመናን በጋረድሁ ጊዜ ቀስቴ በደመናው ትታያለች፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድር ላይ ደመናን በጋረድሁ ጊዜ ቀስቲቱ በደመናው ትታያለች፤ |
በእኔና በእናንተ፥ ሕያው ነፍስ ባለውም ፍጥረት መካከል ያለውን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ፤ ውኃም ዳግመኛ ፍጥረትን ሁሉ ያጠፋ ዘንድ የውኃ ሙላት አይመጣም።