ዘፍጥረት 7:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጥፋት ውኃ በምድር ላይ በመጣ ጊዜ የኖኅ ዕድሜ ስድስት መቶ ዓመት ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጥፋት ውሃ በምድር ላይ በወረደ ጊዜ ኖኅ የስድስት መቶ ዓመት ሰው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጥፋት ውሃ በምድር ላይ በመጣ ጊዜ የኖኅ ዕድሜ 600 ዓመት ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኖኅም የጥፋት ውኃ በምድር ላይ በሆነ ጊዜ የስድስት መቶ ዓመት ዕድሜ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኖኅም የጥፋት ውኂ በምድር ላይ በሆነ ጊዜ የስድስት መቶ ዓመት ዕድሜ ነበረ። |
ኖኅ ስድስት መቶ ዓመት በሆነው፥ በሁለተኛው ወር፥ ከወሩም በዓሥራ ሰባተኛው ቀን ላይ፥ ከምድር በታች ያለው የታላቁ ጥልቅ መፍለቂያዎች ሁሉ በድንገት ተነደሉ፥ የሰማያትም መስኮቶች ተከፈቱ፥
የኖኅ ዕድሜ ስድስት መቶ አንድ በሆነ ጊዜ፥ በመጀመሪያው ወር፥ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን፥ ውኃው ከምድር ላይ ደረቀ፤ ኖኅ የመርከቡን ክዳን አንሥቶ ዙሪያውን ተመለከተ፤ ምድሪቱ እንደ ደረቀች አየ።