የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 6:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለመርከቢቱም ጣራን አብጅለት፤ ከቁመትዋም አርባ አራት ሳንቲ ሜትር ትተህ ጨርሳት፥ መርከቡ ባለ ሦስት ፎቅ እንዲሆን አድርግ፤ በጎኑም በኩል በር አድርግለት።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ለመርከቧ ጣራ አብጅላት፣ ጣራና ግድግዳው በሚጋጠምበት ቦታ ግማሽ ሜትር ክፍተት ተው፤ ከጐኗ በር አውጣላት፤ ባለሦስት ፎቅ አድርገህ ሥራት።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ለመርከቡ ጣራ አብጅለት፤ ጣራውና ግድግዳው በሚጋጠሙበት ቦታ ላይ 44 ሳንቲ ሜትር ባዶ ቦታ ተውለት፤ መርከቡ ባለሦስት ፎቅ እንዲሆን አድርግ፤ በጐኑም በኩል በር አድርግለት፤

ምዕራፉን ተመልከት

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለመ​ር​ከ​ቢ​ቱም መስ​ኮ​ትን ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ ከቁ​መ​ቷም ክንድ ሙሉ ትተህ ጨር​ሳት፤ የመ​ር​ከ​ቢ​ቱ​ንም በር በጎ​ንዋ አድ​ርግ፤ ታች​ኛ​ው​ንም፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም፥ ሦስ​ተ​ኛ​ው​ንም ደርብ ታደ​ር​ግ​ላ​ታ​ለህ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለመርከቢቱ መስኮትን ታድርጋለህ ከቁመትዋም ክንድ ሙሉ ትተህ ጨርሳት የመርከቢቱንም በር በጎንዋ አድርግ ታችኛውንም ሁለተኛውንም ሦስተኛውንም ደርብ ታደርግላታለህ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 6:16
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የመርከቢቱ ርዝመት ሦስት መቶ ክንድ፥ ወርድዋ አምሳ ክንድ፥ ከፍታዋ ሠላሳ ክንድ አድርግ፤


እነሆ፥ እኔ ከሰማይ በታች የሕይወት እስትንፋስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት፥ በምድር ላይ የጥፋት ውኃን አመጣለሁ፥ በምድር ያለ ሁሉ ይጠፋል።


ፍጥረት ሁሉ ወንድና ሴት ሆነው ወደ መርከቡ የገቡት እግዚአብሔር እንዳዘዘው ገቡ፤ ጌታም በስተ ኋላው ዘጋበት።


ከአርባ ቀንም በኋላ ኖኅ የሠራውን የመርከቢቱን መስኮት ከፈተ፥


የጌታ ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ ሲገባ፥ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ሆና ትመለከት ነበር፤ ንጉሥ ዳዊት በጌታ ፊት ሲዘልና ሲያሸበሽብ ባየችው ጊዜ በልቧ ናቀችው።


በዚህም ጊዜ ኢዩ ወደ ኢይዝራኤል ደረሰ፤ ኤልዛቤልም ይህን የሆነውን ነገር ሰምታ ዐይንዋን ተኳለች፤ ጠጉርዋንም ተሠርታ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ላይ በመስኮት አዘንብላ ቁልቁል መንገዱን ትመለከት ነበር።


የቤቱ መግቢያዎች፥ ጠባቦቹ መስኮቶች፥ በዙሪያቸው የነበሩ ሦስት መተላለፊያዎች፥ የቤቱ መግቢያ ዙሪያውን ከመሬት ጀምሮ እስከ መስኮቶቹ ድረስ በእንጨት ተለብጦ ነበር፤ መስኮቶቹም የተሸፈኑ ነበሩ፤


በውስጠኛው አደባባይ በሀያው ክንድ ፊት ለፊት በውጭውም አደባባይ በወለሉ ፊት ለፊት በሦስት ደርብ በትይዩ የተሠራ መተላለፊያ ነበረ።


ባለቤቱ ተነሥቶ በሩን ከቈለፈ በኋላ፥ እናንተ በውጭ ቆማችሁ ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! ክፈትልን’ እያላችሁ በሩን ማንኳኳት ትጀምራላችሁ፤ እርሱም መልሶ ‘ከየት እንደ ሆናችሁ አላውቅም’ ይላችኋል።