ዘፍጥረት 50:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያች ምድር የሚኖሩ የከነዓን ሰዎችም በአጣድ አውድማ የሆነውን ልቅሶ ባዩ ጊዜ፦ “ይህ ለግብጽ ሰዎች ታላቅ ልቅሶ ነው አሉ፥” ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም አቤል ምጽራይም ብለው ጠሩት፥ እርሱም በዮርዳኖስ ማዶ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ የሚኖሩ ከነዓናውያን በአጣድ ዐውድማ የተደረገውን ልቅሶ ባዩ ጊዜ፣ “ይህ ለግብጻውያን መራራ ልቅሷቸው ነው” አሉ። በዮርዳኖስ አጠገብ ያለው የዚያ ቦታ ስም አቤል ምጽራይም ተብሎ መጠራቱም ከዚሁ የተነሣ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያ የሚኖሩ ከነዓናውያን በአጣድ አውድማ ለቅሶውን ባዩ ጊዜ “ይህ የግብጻውያን ለቅሶ እንዴት መሪር ነው?” አሉ። በዚህ ምክንያት በዮርዳኖስ ሜዳ ያለው የዚያ ቦታ ስም “አቤል ምጽራይም” ተባለ፤ ትርጒሙም በዕብራይስጥ “የግብጻውያን ለቅሶ” ማለት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያች ምድር የሚኖሩ የከነዓን ሰዎችም በአጣድ አውድማ የሆነውን ልቅሶ በአዩ ጊዜ፥ “የግብፅ ልቅሶ እንዲህ ታላቅ ነውን?” አሉ፤ ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም “ላሐ ግብፅ” ብለው ጠሩት፤ እርሱም በዮርዳኖስ ማዶ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያች ምድር የሚኖሩ የከነዓን ስዎችም በአጣድ አውድማ የሆነውን ልቅሶ ባዩ ጊዜ፦ ይህ ለግብፅ ሰዎች ታልቅ ልቅሶ ነው አሉ፤ ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም አቤል ምጽራይም ብለው ጠሩት እርሱም በዮርዳኖች ማዶ ነው። |
ያዕቆብም ሌዊንና ስሞዖንን እንዲህ አለ፦ “በዚች አገር በሚኖሩ በከነዓናውያንና በፌርዛውያን ሰዎች የተጠላሁ ታደርጉኝ ዘንድ እኔን አስጨነቃችሁኝ፥ እኔ በቍጥር ጥቂት ነኝ፥ እነርሱ በእኔ ላይ ይሰበሰቡና ይመቱኛል፥ እኔም ከወገኔ ጋር እጠፋለሁ።”
እነዚህ ተራሮች የሚገኙት ከዮርዳኖስ ማዶ ፀሓይ በምትጠልቅበት አቅጣጫ ካለው መንገድ በስተ ምዕራብ በዓረባ በሚኖሩ የከነዓናውያን ምድር ውስጥ ከጌልገላ ፊትለፊት፥ በሞሬ ታላላቅ ዛፎች አጠገብ አይደለምን?
ይህን ዮርዳኖስን አትሻገርምና ወደ ፒስጋ ራስ ውጣ፥ ዓይንህንም አንሥተህ ወደ ምዕራብና ሰሜንም ወደ ደቡብም ወደ ምሥራቅም በዓይንህ ተመልከት።
የወርቅ ዐይጦቹም ቍጥር፥ አምስቱ የፍልስጥኤም ገዢዎች በሚያስተዳድሯቸው የተመሸጉ ከተሞችና ከእነዚህ ውጭ ባሉት መንደሮቻቸው ቍጥር ልክ ነው። በቤትሼሜሻዊው በኢያሱ እርሻ ውስጥ የጌታን ታቦት ያስቀመጡበት ያ ትልቅ ቋጥኝ እስከ ዛሬ ምስክር ነው።