ዘፍጥረት 5:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሄኖክም ስድሳ አምስት ዓመት ኖረ፥ ማቱሳላንም ወለደ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሔኖክ፣ ዕድሜው 65 ዓመት በሆነ ጊዜ ማቱሳላን ወለደ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሔኖክ 65 ዓመት ሲሆነው ማቱሳላን ወለደ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሄኖክም መቶ ስድሳ አምስት ዓመት ኖረ፤ ማቱሳላንም ወለደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሄኖክም መቶ ስድሳ አምስት ዓመት ኖረ፤ ማቱሳላንም ወለደ፤ ሄኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረገ፤ |
ሄኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ተወሰደ፤ እግዚአብሔርም ስለ ወሰደው አልተገኘም። ከመወሰዱም በፊት እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘ ተመስክሮለታል።