ዘፍጥረት 45:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤልም፦ “ልጄ ዮሴፍ ገና በሕይወት ከሆነ ይበቃኛል፥ ሳልሞት እንዳየው እሄዳለሁ” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እስራኤል፤ “ልጄ ዮሴፍ በሕይወት አለ፤ ከመሞቴ በፊት ሄጄ ልየው” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ያዕቆብ “ልጄ ዮሴፍ በሕይወት መኖሩን ካረጋገጥሁ ይበቃኛል፤ ከመሞቴ በፊት ሄጄ አየዋለሁ” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤልም፥ “ልጄ ዮሴፍ ገና በሕይወት ከሆነ ይህ ለእኔ ታላቅ ነገር ነው፤ ሳልሞት እንዳየው እሄዳለሁ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤልም፦ ልጄ ዮሴፍ ገና በሕይወት ከሆነ ይበቃኛል ሳልሞት እንዳየው እሄዳለሁ አለ። |