ዘፍጥረት 43:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም፥ “ሰውየው ስለ ራሳችንና ስለ ቤተሰባችን አጥብቆ ጠየቀን፤ እንደገናም ‘አባታችሁ አሁንም በሕይወት አለ? ሌላስ ወንድም አላችሁ’ ሲል ጠየቀን። እኛም ለጥያቄው መልስ ሰጠነው። ታድያ፥ ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ወደዚህ እንድትመጡ’ እንደሚል እንዴት ማወቅ እንችል ነበር?” ብለው መለሱለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም፣ “ሰውየው ስለ ራሳችንና ስለ ቤተ ሰባችን አጥብቆ ጠየቀን፤ እንደ ገናም ‘አባታችሁ አሁንም በሕይወት አለ? ሌላስ ወንድም አላችሁ?’ ሲል ጠየቀን። እኛም ለጥያቄው መልስ ሰጠነው። ታዲያ፣ ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ወደዚህ እንድትመጡ’ እንደሚል እንዴት ማወቅ እንችል ነበር?” ብለው መለሱለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም “ሰውየው ስለ ራሳችንና ስለ ቤተሰባችን አጥብቆ መረመረን፤ ‘አባታችሁ በሕይወት አለን? ሌላስ ወንድም አላችሁን?’ ብሎ ጠየቀን፤ እኛም ለጥያቄው ተገቢውን መልስ ሰጠን፤ ስለዚህ ሰውየው ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ እንድትመጡ’ እንደሚለን እንዴት ልናውቅ እንችል ነበር?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም አሉ፥ “ያ ሰው ስለ እኛና ስለ ትውልዳችን ፈጽሞ ጠየቀን፤ እንዲህም አለን፦ ‘ሽማግሌው አባታችሁ ገና በሕይወት ነው? ወንድምስ አላችሁን?’ እኛም እንደዚሁ እንደ ጠየቀን መለስንለት፤ በውኑ፦ ‘ወንድማችሁን አምጡ’ እንዲለን እናውቅ ነበርን?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም አሉ፦ ያ ሰው ስለ እኛና ስለ ወገናችን ፈጽሞ ጠየቀን እንዲህም አለን፦ አባታችሁ ገና በሕይወት ነው? ወንድምስ አላችሁን? እኛም እንደዚሁ እንደ ጥያቄው መለስንለት በውኑ፦ ወንድማችሁን አምጡ እንዲለን እናውቅ ነበርነን? |
እነርሱ ግን መልሰው፥ “እኛ አገልጋዮችህ በከነዓን አገር ከሚኖር ከአንድ ሰው የተወለድን ዐሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን። ትንሹ ወንድማችን አባታችን ዘንድ ሲሆን፥ አንዱ ግን የለም” አሉት።