ዘፍጥረት 40:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም፥ “ምነው ዛሬስ ፊታችሁ ላይ ኀዘን ይነበባል?” በማለት አብረውት በጌታው ግቢ የታሰሩትን የፈርዖን ሹማምንት ጠየቃቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም፣ “ምነው ዛሬስ ፊታችሁ ላይ ሐዘን ይነበባል?” በማለት ዐብረውት በጌታው ግቢ የታሰሩትን የፈርዖን ሹማምት ጠየቃቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ዛሬ በፊታችሁ ላይ ሐዘን የሚታየው ለምንድን ነው?” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጌታው ቤት ከእርሱ ጋር በግዞት የነበሩትንም የፈርዖን ሹሞች እንዲህ ብሎ ጠየቃቸው፥ “እናንት ዛሬ ስለምን አዝናችኋል?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጌታው ቤት ከእርሱ ጋር በግዞት የነበሩትንም የፈርዖንን ሹማምት እንዲህ ብሎ ጠየቃቸው፦ እናንተ ዛሬ ስለ ምን አዝናችኍል? |
እርሱም አምኖንን፥ “የንጉሥ ልጅ ሆይ፤ ሰውነትህ ቀን በቀን የሚከሳው ለምንድነው? ለምን አትነግረኝም?” ሲል ጠየቀው። አምኖንም፥ “የወንድሜን የአቤሴሎምን እኅት ትዕማርን አፍቅሬ ነው” አለው።
እርሱም፥ “እንዴት፥ ‘ምን ሆንክ’ ብላችሁ ትጠይቁኛላችሁ? የሠራኋቸውን አማልክቴንና ካህኔን ወስዳችሁ ሄዳችኋል፤ ምን የቀረኝ ነገር አለ?” አላቸው።
ባሏ ሕልቃናም እርሷን፥ “ሐና ሆይ፥ ለምን ታለቅሻለሽ? ለምንስ አትበዪም? ልብሽስ ለምን ያዝናል? ከዐሥር ወንዶች ልጆች እኔ አልበልጥብሽምን?” ይላት ነበር።