ዘፍጥረት 40:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታስረው የነበሩት የግብጽ የንጉሥ የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃና የእንጀራ ቤቱ አዛዥ፥ በአንድ ሌሊት የየራሳቸውን ሕልም አዩ፤ የሁለቱም ሕልም ለየራሱ የተለየ ፍቺ ነበረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታስረው የነበሩት የግብጽ የንጉሥ የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃና የእንጀራ ቤቱ አዛዥ፣ በአንድ ሌሊት የየራሳቸውን ሕልም አዩ፤ የሁለቱም ሕልም ለየራሱ የተለየ ፍች ነበረው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የንጉሡ የወይን ጠጅ አሳላፊና የእንጀራ ቤት ኀላፊ ሁለቱም በእስር ቤት ሳሉ በአንድ ሌሊት ሕልም አዩ፤ የእያንዳንዳቸው ሕልም የተለያየ ትርጒም ነበረው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለቱም በአንዲት ሌሊት ሕልምን አለሙ። በግዞት ቤት የነበሩት የግብፅ ንጉሥ ጠጅ አሳላፊዎች አለቃና የእንጀራ አበዛዎች አለቃ ሁለቱም እየራሳቸው ሕልምን አለሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በግዞት ቤት የነበሩት የግብፅ ንጉሥ ጠጅ አሳላፊና እንጀራ አበዛ ሁለቱም በአንዲት ሌሊት እንደ ሕልሙ ትርጓሜ እየራሳቸው ሕልምን አለሙ። |
እነርሱም “ሁለታችንም ሕልም አየን፤ ነገር ግን የሚተረጉምልን ሰው አጣን” ሲሉ መለሱለት። ዮሴፍም፥ “ሁልጊዜስ ቢሆን የሕልም ትርጓሜ ከእግዚአብሔር የሚገኝ አይደለምን? እስቲ ያያችሁትን ሕልም ንገሩኝ” አላቸው።