ዘፍጥረት 38:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም ተይዛ በምትወሰድበት ጊዜ ለዐማትዋ፥ “እኔ ያረገዝሁት የእነዚህ ዕቃዎች ባለቤት ከሆነ ሰው ነው” ስትል ላከችበት፤ ደግሞም፥ “የማኅተሙ ቀለበት ከነማንጠልጠያውና በትሩ የማን እንደሆነ እስቲ ተመልከት” አለችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም ተይዛ በምትወሰድበት ጊዜ ለዐማቷ፣ “እኔ ያረገዝሁት የእነዚህ ዕቃዎች ባለቤት ከሆነ ሰው ነው” ስትል ላከችበት፤ ደግሞም፣ “የማኅተሙ ቀለበት ከነማንጠልጠያውና በትሩ የማን እንደ ሆነ እስኪ ተመልከት” አለችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም ተይዛ ውጪ በምትወጣበት ጊዜ “እኔ የፀነስኩት የእነዚህ ዕቃዎች ባለቤት ከሆነ ሰው ነው፤ ይህን የማኅተም ቀለበት ከነማሰሪያውና ይህንንም በትር ተመልክተህ የማን እንደ ሆኑ ዕወቅ” ብላ ለዐማቷ ለይሁዳ ላከችለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም ሲወስዱአት ወደ አማቷ እንዲህ ብላ ላከች፤ “ተመልከት፦ ይህ ቀለበት፥ ይህ ኩፌት፥ ይህ በትር የማን ነው? ይህስ ፅንስ የማን ነው?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም ባወጡአት ጊዜ ወደ አማትዋ እንዲህ ብላ ላከች፦ ለዚህ ለባለ ገንዘብ ነው የፀነስሁት፤ ተመልከት፤ ይህ ቀለበት ይህ አምባር፤ ይህ በትር የማን ነው? |
“ታዲያ ምን መያዣ ልስጥሽ?” አላት። እርሷም፥ “የማኅተም ቀለበትህን ከነማሰሪያው፥ እንደዚሁም ይህን በትርህን ስጠኝ” አለችው። የጠየቀችውን ሁሉ ሰጣትና አብሯት ተኛ፤ እርሷም ፀነሰች።
ስለዚህም፥ በጨለማ የተሰወረውን ወደ ብርሃን የሚያወጣ ደግሞም የልብን ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ፥ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ፤ በዚያን ጊዜም እያንዳንዱ ምስጋናው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሆናል።
ሙታንን፥ እንዲሁም ታላላቆችንና ታናናሾችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ ሌላም መጽሐፍ ተከፈተ፤ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት በተጻፈው መሠረት፥ እንደ ሥራቸው መጠን ፍርድን ተቀበሉ።