ዘፍጥረት 36:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዔሳው ልጆች ስም ይህ ነው፥ የዔሳው ሚስት የዓዳ ልጅ ኤልፋዝ፥ የዔሳው ሚስት የባሴማት ልጅ ረዑኤል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዔሳው ወንዶች ስም፦ የዔሳው ሚስት የዓዳ ልጅ ኤልፋዝና የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጅ ራጉኤል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዔሳው ከሚስቱ ከዓዳ ኤሊፋዝን፥ ከሚስቱ ከባሴማት ረዑኤልን ወለደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዔሳው ልጆች ስም ይህ ነው፤ የዔሳው ሚስት የሐዳሶ ልጅ ኤልፋዝ፤ የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጅ ራጉኤል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዔሳው ልጆች ስም ይህ ነው የዔሳው ሚስት የዓዳ ልጅ ኤልፋዝ ሚስት የቤሴሞት ልጅ ራጉኤል። |